የበይነመረብ አስተዳደር ጉባኤ ደህንነቱ የተረጋገጠ የኢንተርኔት አስተዳደር እንዲኖር ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ መሆን እንደሚመገባው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመደ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ

ኢትዮጵያ ያስተናገደችው 17ኛው የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ይፋዊ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የተገኙት ጠቅላይ ሚስትር አብይ አህመድ (ፒ ኤች ዲ) የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ደህንነቱ የተረጋገጠ የኢንተርኔት አስተዳደር እንዲኖር ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ የመፍትሄ ሃሳቦች የሚቀመጡበት መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ አዉጥታ እየሠራች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በትራንስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ ነዉ ብለዋል።ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል።

በቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቶሬዝ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና አካታች የሆነ የበይነ-መረብ ግንኙነትን ተደራሽ ለማድረግ መንግስታት እና የግሉ ዘርፍ በትብብር መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

17 ኛው የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን የመክፈቻ ስነ ስርዓት ዛሬ ተካሂዷል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook