የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ለአፍሪካ የኢንተርኔት ችግሮች መፍትሄ የሚያመላክት መሆን እንዳለበት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

17 ኛው ዓለም አቀፍ የበይነመረብ አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ከጉባኤው ጎን ለጎን የዓለም አቀፉ የበይነመረብ አስተዳደር ጉባኤ ከፍተኛ የመሪዎች መድረክ ተካሂዷል።

ለ2 ዓመት የጉባኤው የከፍተኛ መሪዎች አባሏና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ኢንተርኔትን ለዜጎቻቸው ማዳረስ ላልቻሉ ሀገራት መፍትሄ የሚሆኑ ጉዳዮች የሚኑሱበት እንዲሆን ጠይቀዋል።

በጉባኤው ከፍተኛ መሪዎች የሚነሱ ሃሳቦች ያደጉ ሀገራት ላይ ያተኮሩ ብቻ መሆን የለባቸውም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ አፍሪካውያን ገና ለዜጎቻቸው ኢንተርኔትን የማዳረስ ሩጫ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ጀማሪ እንደመሆናቸው መጠን ኢንተርኔትን ለዜጎች እኩል ማዳረስ ላይ እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነመረብ አስተዳደር ጉባኤ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ነገ ዋናው መክፈቻ ይከናወናል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook