የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ከተሞችን ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ተጨማሪ ግብዓት የሚገኝበት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አበቤ ተናገሩ።

የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ከተሞችን ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ተጨማሪ ግብዓት የሚገኝበት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አበቤ ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ለበይነመረብ አስተዳደር ጉባኤ ተሳታፊ እንግዶች በወዳጅነት ፓርክ የእራት ግብዣ አድርገዋል።

የበይነመረብ አስተዳደር ጉባኤ ዋና አጀንዳ የሆነው “ደህንነቱ የተረጋገጠና ተመጣጣኝ የበይነ-መረም ግንኙነት ማዳረስ” ዘመናዊ ከተማ (Smart city) ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

እንዲህ ያለ ጉባኤ ከተሞችን ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተጨማሪ ግብዓት የሚገኝበት መሆኑን የተናገሩት ከንቲባዋ አዲስ አበባን ዘመናዊ ከተማ (Smart city) ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 17ኛው የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook