የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት የግል ዴታ ጥበቃ አዋጅ ህጎችን ባከበረ መልኩ የሙከራ ስራው እየተከናወነ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የብሄራዊ መታወቂያ የሙከራ ስራ ያለበትን ደረጃ በመመልከት ከፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል።

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት በሙከራ ደረጃ በተለያዩ የፌደራል የመንግስት ተቋማት ላይ እየተተገበረ ይገኛል።

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል በ2018 ዓም ህፃናትን ሳይጨምር 95 ከመቶ ለሚሆኑ ዜጎች መታወቂያውን ለማዳረስ ይሰራል ብለዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ፍትሃዊ አሰራርን ለመዘርጋትና ዜጎች በኦንላይን አገልግሎት ላይ ያላቸውን እምነትን ለመጨመር ብሄራዊ መታወቂያ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

ለዜጎች የመረጃ ጥበቃ ልዩ ትኩረት መሰጠት አለበት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለፕሮጀክቱ ስኬት ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገለፀዋል።

መታወቂያው በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀውንና በመፀደቅ ሂደት ላይ ያለውን የግል ዴታ ጥበቃ አዋጅ የሚደነግጋቸውን ህጎች ባከበረ መልኩ የሙከራ ስራው እየተሰራ ይገኛል ተብሏል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook