የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር 6 አገልግሎቶቹን ኦንላይን መስጠት ጀመረ።

አገልግሎቶቹ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የለሙ ሲሆን የፈሳሽ አገልግሎት ቦቴ ትክክለኛነት ማረጋገጫ፣ ድጋሚ ትክክለኛነት ማረጋገጫ፣ ምትክ ማረጋገጫ፣ ምትክ መለያ ቁጥር፣ የሚዛን ልኬት ትክክለኛነት ማረጋገጫና ምትክ ማረጋገጫ አገልግሎቶች ናቸው።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለ መኮንን የፈሳሽ ጭነት አገልግሎት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ለመፍታት እና ፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አገልግሎቶቹ በኦንላይን መሰጠታቸው ግልፅ፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር እንዲኖርና ተገልጋዩ በከፈለበት ልክ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ዜጎች የመንግስት አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ባሉበት ሆነው እንዲያገኙ ለማድረግ መንግስት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን በ25 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት 282 የሚጠጉ አገልግሎቶች ለምተው በስራ ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ በዚህ አመት 400 የመንግስት አገልግሎቶችን ኦንላይን ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል።

የለሙት ሰርዓቶች ሳይቆራረጡ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook