የአፍሪካ ሀገራት ግልፅ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ሊኖራቸው ይገባል:- ሁሪያ አሊ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ

አፍሪካ ትሪቡን ከሁዋዌ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት “የአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚ ጉባኤ” በበይነ-መረብ ተካሂዷል።

ጉባኤው የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪዎች፣ ባለሙያዎች፣ መሪዎችና የግል ድርጅት አንቀሳቃሾች በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦችን ማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንዲመክሩ የተዘጋጀ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎቻቸውን በዲጂታል ኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረ ግልፅ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

አካታችነች፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እና የስራ ፈጠራን ያካተተው “የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን” በተመለከተ ለመድረኩ ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታዋ የአፍሪካ ሀገራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ኢኖቬሽን ላይም ማተኮር አለባቸው ብለዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለም ኢኮኖሚ እድገት ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድርም የዲጂታል ኢኮኖሚው እንዲፋጠን እገዛ ማድረጉ ተንስቷል።

የአፍሪካን የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት ማፈጠን ላይ ትኩረቱን ባደረገው በዚህ ጉባኤ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ሃላፊዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook