ኢትዮጵያ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ እና ከአስር ዓመት የልማት ዕቅድ ከመሳሰሉ ቁልፍ አገራዊ ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣመ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ማዘጋጀት ፀድቆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ስትራቴጂው አህጉራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂን ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ስትራቴጂዎች ጋርም የተሰሳረ ነው፡፡
ይህን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት በኩል ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፡፡
ኢትዮጵያ የፕሮጀክት ድጋፉ ጸድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ ለማድረግ የሚያግዙና የሚያቀላጥፉ የአካባቢያዊና የማኅበረሰባዊ ቁርጠኝነት (Environmental and Social Commitment Plan) እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እቅዶችን (Stakeholder Engagement Plan) አዘጋጅታለች።
ሰነዶቹ ለህዝብ ይፋ ስለሆኑ ሙሉ መርጃውን በሚቀጥሉት ማስፈንጠሪያዎች ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እቅድ https://mint.gov.et/docs/stakeholder-engagement/?lang=en የአካባቢያዊና የማኅበረሰባዊ ቁርጠኝነት እቅድ https://mint.gov.et/docs/environmental-and-social-commitment-plan-escp-for-ethiopia-digital-foundations-project/?lang=en
ኢትዮጵያ የዲጂታል እድሎችን በመጠቀም የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየሰራች ትገኛለች፡፡