የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየተሰራ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቶኒብሌር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከአይሲቲና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቲጂው በመጀመሪያ የትግበራ ጊዜያት ያጋጠሙ ችግሮች እየተወሰዱ ያሉ የመፍትሄ እርምጃዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ስትራቴጂውን ወደ ተግባር ለመቀየር በተቋም ውስጥ በቡድን የመስራት ልምድን ማዳበርና ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ባለሙያዎቹ የዲጂታል ስትራቴጂውን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የዲጂታል አሰራሮችን በመተግበር የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የተዘጋጀ ነው።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook