የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች የዲጂታል አሰራሮች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ጥናት ኢንስቲትዩት አዲስ ተቀጣሪ ተመራማሪዎች ስለ ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ገለፃ አድርጓል።

ገለፃው እንደ ስትራቴጂክ ጥናት ተመራማሪ ስለ አለም-ዓቀፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ማወቅ ያለባቸው ክህሎቶች ላይ መነሻ የሚሆን ሃሳብ ለማስጨበጥ ያለመ ነው።

ገለፃውን ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ (ፒ ኤች ዲ) ተመራማሪዎቹ ለዲጂታል አሰራር ትኩረት በመስጠት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ዝርዝር ቴክኒካል ስልጠናዎችንም በቀጣይ በተከታታይ ለመስጠት መታቀዱንም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል አሰራሮችን በመተግበር የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook