የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን ለማሳለጥ የኢንተርኔት አስተዳደር ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን፣ ኢንተርኔት ሶሳይቲ፣ አይሲቲ-ኢቲ ከፕሪዳ (የፖሊስና ቁጥጥር ኢኒሺየቲቭ ለዲጂታል አፍሪካ) ከተሰኘውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢንተርኔት አስተዳደር ስልጠና ተጀምሯል፡፡

የስጠናው ዓላማ በዘርፉ ላሉና ከመንግስት፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙኃን፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ተማሪዎችና ከዘርፉ ማኅበረሰብ ለተውጣጡ የተለያዩ ሰዎች በአንተርኔት አስተዳደር ዙሪያ አቅማቸውን መገንባት ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል አቢዮት ሲናሞ (ፒ ኤች ዲ) የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ ጉዞ ለማሳለጥ የኢንትርኔት መሰረተ ልማት ማስፋፊያ፣ የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ልማትና የዲጂታል እውቀት ላይ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን ለማሳለጥ የኢንተርኔት አስተዳደር ወሳኝ ነው ያሉት ዳይሬከተር ጀነራሉ ለውጤታማነቱም የበይነ መረብ ግንኙነትን ማሳደግና መጠቀም እንዲሁም የኢንተርኔት አስተዳደር ላይ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

በስልጠኛው ለመሳተፍ ከ300 በላይ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ የመመልመያ መስፈርቱን ያሟሉ 50 ሰዎች በስልጠናው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook