ስምምነቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማእቀፍ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት እና ፖሊሲ ለመደገፍ የሚያስችል ነው ።
የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለግሉ ዘርፍ የተመቸ ማድረግ እና የግሉም ዘርፍ ተገቢዉን አስተዋጽኦ እንዲያረግ ማድረግ የሁለቱም አገሮች ፍላጎት መሆኑ በስምምነቱ ተገልጿል።
ትብብሩ በተለይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በዲጂታል ኢኮኖሚዉ ዉስጥ በሚገባ እንዲሳተፉ ማስቻል ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል ።
ስምምነቱን በጀርመን መንግሥት በኩል የጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዬች እና ኢነርጂ ምክትል ሚንስትር ሚስተር ቫንደርቪትዝ የፈረሙ ሲሆን በኢትዮጵያ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ን በመወከል ደግሞ በጀርመን የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ፈርመዋል።