የኢትዮ-ራሺያን የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክ፣ የቴክኒካልና የንግድ ትብብር ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽን ውይይት…

የኢትዮ-ራሺያን የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክ፣ የቴክኒካልና የንግድ ትብብር ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽንን በጋራ ሊቀመንበርነት የሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክቡር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) እና የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ክቡር ሚ/ር ኤቭጅኒ ፔትሮቭ (Evgeny Petrov) በበይነ መረብ ትውውቅና ውይይት አደረጉ።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ የኢትዮጵያና ራሺያ የጋራ ሊቀመንበሮች ለሰባት ጊዜ የኢትዮ-ራሺያ የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክ፣ የቴክኒካልና የንግድ ትብብር ኮሚሽን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ የወቅቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ለስምንተኛው የጋራ ጉባኤ የቅድመ ዝግጅትና የትውውቅ ውይይት ከማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ክቡር ሚ/ር ኤቭጅኒ ፔትሮቭ (Evgeny Petrov) ጋር አድርገዋል።

ሰባተኛው ኢትዮ-ራሺያ ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽን ውይይት በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ከጥቅምት 1-3 2019 እ.አ.አ. እንደተካሄደ ይታወቃል። ውይይቱ ትኩረት ያደረገበት ጉዳይም በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያሉትን የሁለትዮሽ የንግድ፣ የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክና የቴክኒካል ትብብሮችን ስለማጠናከር ነበር።

ኢትዮጵያና ራሺያ በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የራሺያ መንግስት አቶሚክ ኢነርጂ ትብብር (ROSATOM) በጥቅምት 24 2019 እ.አ.አ. የተፈረመ ሆኖ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኒውክለር ኢነርጂ ስልጠና ለመስጠት በሚያዚያ 15 2021 እ.አ.አ. የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል።

በተመሳሳይም ኢትዮጵያና ራሺያ፣ በትምህርት፣ በኢነርጂ፣ በጤና፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና በሌሎችም ጉዳዮች በትብብር ይሰራሉ።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook