የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና “ኢንተርኔት ሶሳይቲ” በገጠር የበይነ-መረብ ግንኙነትን (ኢንተርኔት) ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የተጀመረውን ስራ የሚደግፍ፣ በገጠር ጠንካራ የበይነ መረብ ግንኙነትን ለማዳረስ፣ የበይነ መረብ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና የበይነ መረብ አስተዳደርን ለማሳደግ የሚያስችል ነው።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) እና የኢንተርኔት ሶሳይቲ የአፍሪካ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ዳዊት በቀለ (ፒ ኤች ዲ) ፈርመውታል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) አካታች ብልፅግናን ማረጋግጥን ግቡ አድርጎ የተዘጋጀው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እውን እንዲሆን መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የልማት ድርጅቶችና ማህበራት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ስትራቴጂው መሰረተ ልማቶችን ማሟላት፣ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ማልማት እና ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታን መፍጠር የሚሉትን ስለማካተቱም አብራርተዋል።

ስምምነቱ ይህንን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ብለዋል።

የኢንተርኔት ሶሳይቲ የአፍሪካ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ዳዊት በቀለ (ፒ ኤች ዲ) ስምምነቱ የገጠር የበይነ መረብ ግንኙነትን በማሳደግ በገጠር ያለ ሁሉም ማህበረሰብ በዲጂታል ለውጥ ውስጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል።

የኢንተርኔት ሶሳይቲ የዲጂታል የኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራን ለመደግፍ ቁርጠኛ መሆኑም አረጋግጠዋል።

ስምምነቱ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ቅድሚያ የተሰጣቸውን የግብርና፣ የማምረቻ፣ የአገልግሎትና ቱሪዝም ዘርፍን ለመደገ ያግዛል ተብሏል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook