የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር (ፖርታል) ሊያለማለት ነው።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደሩ የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድንን መረጃ ለደጋፊዎቹና ለማህበርሰቡ ባሉበት ለማድረስ የሚያስችል ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) ከፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ስራ አስኪያጅና የቦርድ አመራሮች ጋር ቡድኑን የዲጂታል ፖርታል ባለቤት ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደሩ ከፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ሊንክድኢን ከመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ከቴሌ ብር ጋር በማገናኘት አገልግሎት መስጠት የሚያስችልም ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) ታሪካዊውን የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር በአንድ ወር ጊዜ አልመተን እናስረክባለን ብለዋል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ጉዞ ወደ ሁሉም ዘርፎች ለማውረድ እንሰራለንም ብለዋል።

የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሃኑ ባለሙያዎችን በማሟላት የመረጃ አስተዳደሩ ሳይቆራረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር ስርዓቱ የክለቡን ታሪክ፣ ዕለታዊ የእንቅስቃሴ መረጃ፣ የገቢ ማስገኛ ሽያጭ፣ የደጋፊዎች መረጃ፣ ድጋፍ ማሰባሰቢያና የመሳሰሉትን መረጃዎች አስተሳስሮ ይይዛል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook