የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር የማጠቃለያ ወይይት አድርገዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አመራሮች እና ባለሙያዎች ከ ጥር 23-26/05/2014 ዓ.ም በ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና በተጠሪ ተቋማት በመገኘት ከዘርፉ አመራሮች ጋር ውይይት እና የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

በማጠቃለያ ውይይቱ ላይ ክቡር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ሚኒስቴር መስረያቤቱ በሀገር ደረጃ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት ለማሳካት እንዲሁም በዘርፉ ስራንና ሀብትን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ለክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማት አስፈላጊውን አቅም የመገንባት ስራዎች ይሰራል ብለዋል፤ አክለውም በጋራ የሚከናወኑ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ተግባራትን በመለየት በትብብርና በቅንጅት ተጠናክረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

የሀረሪ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጄንሲ ለማጠናከር በሰው ሃይል ልማት፣ በአሰራር ስርአት ዝርጋታ፣ የዘርፉን መሰረተ ልማት እና የኤጄንሲውን አደረጃጀት በማጠናከር ዙሪያ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም የሁሉም ክልል እና ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማት አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተገኙበት ዘርፉ ውጤታማ በሚሆንበት ሁኔታ ምክክር የሚደረግ መሆኑንና የሚኒስቴር መስሪያቤቱ አመራሮችም በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በመገኘት ተቋማትን በመጎብኘት ያሉበትን ደረጃ የመለየትና የመደገፍ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል፡፡

የሀረሪ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል ኢብራሂም በዘርፉ ስለተደረገላቸው የልምድ ልውውጥ እና ውይይት የሚኒስቴር መስሪያቤቱን እና የተጠሪ ተቋማትን አመራሮችና ባለሙያዎችን አመስግነው፣ በልምድ ልውውጥና ውይይት ያገኙትን ጉዳዮች ኤጄንሲው ወደ ተግባር ለመቀየር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል ብለዋል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook