የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2015 በጀት ዓመት እቅድ የዘርፉ ተዋንያን የሚጨምሯቸው እሴቶች ተለይተው ሊቀመጡ ይገባል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ አመራር አባላት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2015 በጀት ዓመት እቅድና የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክቡር ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒኤችዲ) የ2015 በጀት እቅድ ከነባሩ አመራር የተረከብነው ቢሆንም፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማረጋገጥ፣ ተስማሚና ተወዳዳሪ የዲጅታል ኢኮኖሚ ለመገንባት፣ በሀገር ደረጃ የተቋማትን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና ባህል ለማዳበር፣ ለአዳዲስ ፈጠራዎችና አሰራሮች ትኩረት ሰጥተን ለመስራት ጥረት አድርገናል።

ዶክተር በለጠ አክለውም የበጀት ዓመት የክዋኔ ሂደቶ በዘርፉ አመራር ተገቢ ልምድ ያስገኘና ለ2015 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅትም አቅም የፈጠረ ነው ብለን እናምናለን። ቢሆንም በሦስተኛው ሩብ ዓመት ካደረግነው ግምገማ ከተገኙ ግብአቶች ጠቅላላ አፈጻጸማችን ምን አካቶ አሳካ? ለ2015 በጀት ዓመት ልንጨምረው ስለሚገባ እሴት በሚያሳይ መልኩ አፈጻጸሙና እቅዱ በትኩረት ይገመገማል ብለዋል።

የ2015 በጀት ዓመት እቅዳችንን ላይ ልንጨምርበት የሚገባቸውን እሴቶች በመለየት እንደ አመራር መግባባትና የተቋሙ ጠቅላላ ሠራተኞች እና ቁልፍ ባለሙያዎችን አቅም ልናዳበርብት ስለሚገባ የውይይቱ የትኩረት ማዕከል ነው። ስለሆነም አጠቃላይ አመራሩ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ ለጠቅላላ ሠራተኛው ለማውረድ የየራሱን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል ብለዋል።

በመድረኩ የ2015 በጀት ዓመት ተግባራት አፈጻጸምና የተገኙ ውጤቶች፣ ከእቅድ ክለሳ በኋላ የታዩ ጥንካሬዎች፣ በእቅድ አፈጻጸም ሂደቱ የነበሩ ክፍተቶች ቀርበው ውይይት ተደርጓል። በተጨማራም በበጀት ዐመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከር፣ እጥረቶችን በማረም አዳዲስ እሴቶችን በመጨመር በ2015 በጀት ዓመት ሊካቱቱ የሚገባቸው ነጥቦች ተነስተው ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን በቀጣይ በሚኖሩ ተግባራት ላይ የስራ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook