የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሐብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር የዘርፉን የ2014 ዓ.ም ዕቅድ እና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒርትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የዘርፉን የ2014 ዓ.ም ዕቅድና የሩብ አመት አፈጻጸም ሪፓርት በተመለከተ ገለጻ አቅርበዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በገለጻቸው የዘርፉን ርዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ከተዘጋጀው የ10 አመት ዕቅድ የተቀዳውን የ2014 ዓ.ም እቅድ በዝርዝር አቅርበዋል።

የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርትም እንዳሁ በሚኒስትሩ ቀርቧል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በበኩላቸው የዘርፉ ተልዕኮ ሴክተር ተሻጋሪ ስለሆነ የቅንጅት አሰራሮች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጨማሪ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ጠቁመው ቋሚ ኮሚቴው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ረገድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በተጨማሪም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተለይ ለግብርና፣ ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለቱሪዝም እና ለዲጂታል አገልግሎቶች ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራቸውን ስራዎች በተጨማሪም በትምህርት፣ በስራ ፈጠራ፣ በማዕድን፣ በኢነርጅና ሌሎች ዘርፎችም በትብብር የሚሰራቸውን ስራዎች ሊያጠናክር ይገባዋል ብለዋል።

ክቡር ሚኒርትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አመሰግነው ቅንጅታዊ አሰራሮች እንዲጎለብቱ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ተቋሙ የሚያደርገውን ጥረት ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር የቋሚ ኮሚቴው አስፈላጊ ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘርፉን ርዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በትጋት ይሠራል ብለዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook