የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፋኖስ ለሁሉ በጎ አድራጎት ጋር በመተባበር ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ምግብ፣ አልባሳት፣ የንፅህና መጠበቂያና የመመገቢያ እቃዎችን ያካተተ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በተጠሪ ተቋማትና በፋኖስ የበጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝነት የተሰበሰበው የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ከ500ሺ ብር በላይ ግምት ያለው ነው።

የሚኒስቴሩ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ የተጠለሉ ነፍሰጡሮች፣ የወለዱ እናቶች፣ ሴቶችና አረጋውያንን ጎብኝተዋል።

በከተማዋ ከ200 ሺ በላይ ሰዎች ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች የሚኖሩ ሲሆን ከ18ሺ በላይ የሚሆኑት በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች የተጠለሉ ናቸው ተብሏል።

በደብረ ብርሃን ከተማ ካሉ 22 የትምህርት ተቋማት ውስጥ 6ቱ የስደተኞች መጠለያ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook