የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የ100 ቀን እቅዱን የመራበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ገለፀ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ይህንን ያለው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የ100 ቀን ዕቅድ አተገባበር ላይ ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ፒ ኤች ዲ) ተቋሙ የ100 ቀን እቅዱን የመራበትና በየ 15 ቀኑ የድርጊት መርሃግብር አውጥቶ የመራበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

የቀጣይ 100 ቀን እቅዶችን ላይ ይህንኑ አሰራር አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) እንደ ቴክኖሎጂ ተቋምነታችን እቅዶቻችንን በዲጂታል አሰራር ክትትልና ግምገማ እያደርግን እየሰራን ነው ብለዋል።

ይህንን ልምድ ለሌሎች ተቋማት ለማጋራትም ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

በዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት በማጎልበት የዕቅድ አፈፃፀም ብቃትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሳደግ መንግስት ትክክለኛውን ተግባር በአግባቡ እየከወነ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ብቸኛው ስልት ነው ተብሏል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook