የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአሊባባ ግሎባል ኢኒሼቲቭስ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ለኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች የተሰናዳ የስልጠና መርሃ ግብር ተጀመረ

ስልጠናው ለ52 ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች፣ በንግድ ስራ ለተሰማሩ ግለሰቦች እና ሥራ ፈጣሪዎችን ለሚደግፉ የመንግሰት ሰራተኞች የሚሰጥ ሲሆን ለአንድ ወር የሚቆይ ነው፡፡

ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዳዲስ እድሎችን ፈጥሮ የንግድ ስራን ወደ ላቀ ደረጃ የማሳደግ ክህሎትን በማስጨበጥ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ  አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) ሰልጣኞቹ አድሉን ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል፡፡

ከሰልጣኞቹ መሀከል አንዷ የሆነችውና በሥራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን የአዳዲስ የሥራ እድል ፈጠራና ፕሮጀክት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሪት ቅድስት ከፈለኝ ስልጠናው በአነስተኛ የንግድ ሥራ የተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች ንግዶቻቸውን ወደ ኢንተርፕራይዝነት ለመለወጥ የሚችሉበትን መንገድንም ያመላክተኛል የሚል እምት አለኝ ብላለች፡፡

ስልጠናው የአሊባባን ምርጥ ተሞክሮዎችና ያለፉ ስህተቶች፣  አዲስ ቴክኖሎጂ እና አቅም ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ስለሚያበረክተው አስተዋፅኦ የቻይናን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እንደ አብነት በመውሰድ ቁልፍ ተሞክሮዎችን ያጋራል።

ሥልጠናውን ያጠናቀቁ ተሳታፊዎች በቀጣይ በቻይና በሚደረገው የ 5 ቀናት ስልጠና ላይ እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ።

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ትግበራን ለማገዝ ከአሊባባ ጋር በመተባበር በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በሥራ ፈጠራ ዙሪያ ተመሳሳይ ስልጠናዎችን ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook