የኢኖቬሽኖና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለአገራዊ የባዮቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት አስፈላጊውን እገዛ አደርጋለሁ አለ።

የቀጣይ 10 ዓመታት የባዮቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት መርሃ ግብር ዝግጂት ላይ የሚመክር አገራዊ ዎርክሾፕ በኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና በኢቲዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ትብብር እየተካሄደ ነው።

በወርክሾፑ የኢኖቬሽን ልማትና ምርምር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ባይሳ በዳዳ(ፒኤ ች ዲ) መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደ ዶክተር ባይሳ በወርክሾፑ ላይ የቀርቡት ጥናታዊ ጽሁፎች የሃገራችን እድገት በሚፈለገው መጠን ፈጣንና ቀጣይነት እንዲኖረው እና ለሁለንተናዊ ብልጽግና አበርክቶ ያላቸውን ጠቀሜታ እና አስተዋጽኦ የጎላ ነው።

በተለይም ጥናትና ምርምሮቹ በዘርፉ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት ላይ አተኩረው ሲተገበሩ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አውስተው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ይህንን ሀገራዊ ጠቀሜታ ያለውን የባዮ ቴክኖሎጂ ምርምርና ጥናት በላቀ ደረጃ ለመደገፍ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

ክቡር ዶክተር ባይሳ አክለውም ሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚደግፈው የመንግስት ተቋማትን ብቻ አይደለም። በዚህና በመሰል ምርምር እና ጥናት የሚሳተፉ የግል ሴክተሮችንም ተሳትፎ በመደገፍ ለሃገር እድገት የሚጠበቅባቸውን አበርክቶ እንዲወጡ ለማስቻል በተሳትፏቸው ሁሉ ተጠናክረው እንዲንቀሳቀሱና ውጤታማ እንዲሆኑ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለይ ለዚህ ዐላማቀፋዊ ጠቀሜታ ላለው የባዮቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት የሰጡትን ትኩረትም አመስገነዋል፡፡

በወርክሾፑ “Treneds in Biotechnology Development, Biotechnolgy Research for Development Landscape in Ethiopia, Opportunities and Challenges,10 Years National Biotechnology Research & Developmdnt program” በሚሉ ርዕሶች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook