የኢፌዴሪ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የደቡብ አፍሪካ መንግስት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈርመዋል።

ስምምነቱ የተፈረመው በሁለቱ አገራት በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች በጋራ ለመስራት ነው።

ክቡር ዶክተር አብርሐም በላይ በውይይቱ ወቅት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ሂደት ላደረጉት አወንታዊ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይ ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፣ በአርተፍሻል ኢንተለጀንስ፣ በባዮቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ፣ በስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፣ በስታርት አፕ ድጋፍ እና ሌሎች ተመሳሳይ ልምዶች የምንወስድበት በጋራ ተባብረን የምንሰራበት መግባብያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የደቡብ አፍሪካ ልዑካን በሁለቱ አገራት የጋራ የልማት ጉዳዮች በትብብር ለመስራትና ተናጠላዊ የሠላም እና የፓለቲካ አጀንዳዎችን ሉዓላዊነትን ባከበረ መልኩ በውይይትና በመደጋገፍ መፍታት ላይ አተኩሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook