የኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የትምህርት ስርዓትንና የሥራ ፈጠራን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት አደረጉ።

የኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የትምህርት ስርዓትንና የሥራ ፈጠራን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት አደረጉ።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ፈርመውታል። ስምምነቱ የስራ ፈጠራንና የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን የትምህርት ስርዓት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ዝርዝር ተግባራትን የያዘ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ስምምነቱ ላይ የተቀመጡት ዝርዝር ስራዎች ቁልፍ ጉዳዮችን የያዙ በመሆናቸው ለተግባራዊነቱ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ክህሎት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራት ስምምነቱ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ለዲጂታል ኢኮኖሚው ግንባታ ስኬት የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት ያለው ዜጋ ማፍራት ወሳኝ በመሆኑ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት ክህሎት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራት መስራት ይገባል ተብሏል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook