የከተሞችና ተቋማት ፖርታሎች የዜጎች ታማኝና የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ሊሆኑ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለ5 ከተሞችና ለ6 የፌደራል ተቋማት ፖርታሎችን በማልማት አስረክቧል።ጅግጅጋ፣ ሀረር፣ ጋምቤላ፣ ጅማ እና ሆሳዕና የከተማ ፖርታል የለማላቸው ከተሞች ናቸው።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ፖርታል የለማላቸው የፌደራል ተቋማት ናቸው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የመንግስት አገልግሎቶችን በሂደት ወደ ዲጂታል የአስራር ዘዴ የሚቀየሩበትን ስልት በመንድፍ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል።

የከተሞችና ተቋማት ፖርታሎች የዜጎች ታማኝና የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ሊሆኑ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ባለሙያዎች ፖርታሎቻቸው የዳበረና አዳዲስ መረጃ እንዲይዙ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ፖርታሎቹ የከተሞቹንና የተቋማቱን ልዩ አወቃቀራቸውን፣ አገልግሎቶቻቸውን እና የቱሪስት መስህቦችንና አጠቃላይ መረጃዎችን የያዙ ናቸው። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፖርታል የመረጃ አስተዳደርና አጠቃቀም ስልጠና ለህዝብ ግንኙነትንና የአይሲቲ ባለሙያዎች፣ የፖርታል ልማት ቴክኒካል ስልጠና ደግሞ ለአይሲቲ ባለሙያዎች ሰጥቷል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook