የካንሰር በሽታን የመከላከል አቅምን ለማሻሻል በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ ዳይሬክተር የተነደፈ ተነሳሽነት በይፋ ተመረቀ።

የካንሰር በሽታን የመከላከል አቅምን ለማሻሻልና የአፍሪካ ሀገራትን ቅድሚያ ተጠቃሚ ለማድረግ የተነደፈው የዳይሬክተሩ ኢኒሼቲቭ በአፍሪካ ህብረት ግቢ ውስጥ ተመርቋል።

ኢኒቬቲቩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ)፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር፣ የሴኔጋል፣ የማላዊ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ካንሠርን ለመከላከል የተቀረፀውን ይህንን ኢኒሸቲቭ ለስኬት እንዲበቃ እንደሚሰሩ በመግለፅ ከአለማቀፍ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ ጋር ስምምነት ፈርመዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተነሳሽነቱ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብቻ የሚገኘውን የካንሰር የጨረራ ህክምና በማስፋት ሀገራችንን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ከአለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ የአለምአቀፉ የአቶሚክ ኢነርጅ ተቋም በኢትዮጵያ በእርሻ፣ ጤና፣ ትምህርት እንዲሁም በተለያዩ የልማትና የኢኮኖሚ ዘርፎች ለሚሠራው ስራ ቀዳሚ የመገናኛ ቢሮ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook