የወጣቶችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ በኢትዮጵያ የተገነባው ‹‹ኦሬንጅ ዲጂታል ማዕከል›› ተመርቆ ስራ ጀመረ፡፡

በአፍሪካ ከሴኔጋልና ቱኒዚያ ቀጥሎ በአዲስ አበባ የተገነባው ኦሬንጅ ዲጂታል ማዕከል ተመርቆ ስራ ጀምሯል፡፡

ማዕከሉ ወጣቶች የፈጠራ ስራቸውን የሚያዳብሩበት፣ የሚያስተዋዉቁበትና የሚሸጡበት ነው፡፡

በአይሲቲ ፖርክ ውስጥ የተገነባው የዲጅታል ማዕከሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ፒ ኤች ዲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ፤ የኦሬንጅ ድጂታል ማዕከል ሃላፊዎች እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ስራ ጀምሯል፡፡

ማዕከሉ በኢትዮጵያ የወጣቶች የዲጂታል እውቀት እንዲዳብር፣ በሀገራት መካከል የዲጂታል እውቀትና ልምድ ልውውጥ እንዲጎለብት እድል እንደሚፈጥር የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ፒ ኤች ዲ) ተናግረዋል፡፡

በኦሬንጅ ቴሌኮም የገንዘብ ድጋፍ የተገነባው የዲጂታል ማዕከሉ ለወጣቶች የአይሲቲ የልህቀት ማዕከል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አገልግሎቱንም በነጻ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የወጣቶች ዲጂታል እውቀት ማሳደጊያ ማዕከሉ የኮዲንግ ክፍል፣ የንድፍ ስራ ማበልፀጊያና ወደ ገበያ ማቅረቢያ ክፍሎችን የያዘ ነው፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook