የውድድር ጥሪ ማስታወቂያ!!!


የውድድር ጥሪ ማስታወቂያ!!!

ሚኒስቴር መስሪያቤታችን ከጃፓን ዓለምአቀፍ ትብብር ኤጀንሲ(JICA) ጋር በመተባበር ዱባይ ላይ በየዓመቱ ለሚካሄደው GITEX ኤክስፖ መስፈርቱን የሚያሟሉ የቴክኖሎጂ ስታርታፕ አመልካቾችን አወዳድሮ አሸናፊዎችን ማሳተፍ ይፈልጋል።

ኤክስፖው ስታርትአፖችና ኢንቨስተሮች ትስስር የሚፈጥሩበት መድረክ ሲሆን ከመስከረም 29 – ጥቅምት 5/ 2015 ዓ.ም ለ7 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።

በመሆኑም በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታልና አይሲቲ፣ ቱሪዝም፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ማአድን ዘርፍ ላይ የተሰማራችሁ ቴክኖሎጂ ስታርትአፖችን ተመዝግባችሁ እንድትወዳደሩና ቀኤክስፖው እንድትሳተፉ ጥሪ ያቀርባል፡፡

አመልካቾቸ ማሟላት ስላለባቸው መስፈርቶች
• ደርጅቱ /ስታርታፑ ህጋዊ ሰውነት ያለው መሆኑን
• ደርጅቱ ከአንድ ዓመት ያላነሰና ከሰባት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ እየሰራ ያለ ስለመሆኑ

• ደርጅቱ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ
• ለትርፍ፣ የድህረ ምርት፣ የድህረ ንግድ በትንሹ ለስድስት ወር ቀጣይነት ያለው ገቢ እያገኘ ስለመሆኑ እና በፍጥነት የማደግ ችሎታ ያለው ስለመሆኑ የሚያሳይ መረጃ

• ደርጅቱ በእድገት ላይ ያለ እና ገቢ እያገኘ ስለመሆኑ
• ደርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሮ ከፍቶ እየሰራ ስለመሆኑ
• የደርጅቱ አባላት ከፕሮግራሙ መጀመሪያ እስከ ፍፃሜ ድረስ በንቃት መከታተል ያለባቸው ስለመሆኑ
• የደርጅቱ አባላት የታደሰ ፓስፖርት ያላቸውና ወደ ዱባይ መጓዝ የሚችሉ ስለመሆናቸው

አመልካቾች
ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለሁለት ሳምንት በሚቀጥለው ሊንክ https://forms.gle/krxG19yYVu5yqkoYA መመዝገብ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 251911661675፣251910536332 እና 251934824675 ይደውሉ

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook