የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የእንግሊዝ ተራድኦ ድርጅት(FCDO) ደጋፍ የሚያደርጉለት የኢኖቬሽን ለልማት ፕሮግራም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው ተግባራዊ እየተደረገ ያለው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ማዕቀፍ ውስጥ የኢንደስትሪውን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ውጤታማ የምርምር ውጤቶችን ወደ ገበያ ለማስገባት የሚያስችላቸውን የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ያስችል ዘንድ የመጨረሻውን ውድድር እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ውድድር ከሀያ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡት አርባ ዘጠኝ ውጤታማ፣ የተጠናቀቁ እና ወደ ገበያ ሊገቡ የሚችሉ የምርምር ውጤቶች ቀርበዋል፡፡ በመጀመሪያውን ዙር ውድድር ያለፉ አስራ አንድ(11) ፕሮጀክቶች የመጨረሽውን ውድድር እያካሄዱ ነው፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀገራዊ የምርምር ስራዎች ወደ ገበያ ገብተው የኢንዱስትሪውን ችግር በመፍታት ምርታማነትን የሚጨምሩ እንዲሆኑ ለማስቻል ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ይህ የምርምር ውጤቶችን ወደ ገበያ ማስገቢያ የድጋፍ ስርዓት አንዱ ነው።
በቀጣይም እንዲህ አይነት ድጋፎች በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት እና የምርምር ተቋማት ተጠናከሮ ይቀጥላል፡፡