ለፌደራል የመንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የ‹‹መሰረታዊ የዲታላይዜሽን አቅም ግንባታ›› ስልጠና ተጠናቅቋል፡፡
ስልጠናው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር EDACY ከተሰኘ የዲጂታል ስልጠና እና አቅም ግንባታ አቅራቢ ኩባንያ ጋር በመተባበር ነው ሲሰጥ የቆየው፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ጀነራል አቢዮት ባዩ (ፒ ኤች ዲ) ያለ ዲጂታል ክህሎት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማሳካት ስለማይቻል የመንግስት ሰራተኞች የዲጂታል እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ገልፀዋል።

ሰልጣኞች ባገኙት የዲጂታል እውቀት መሰረት ለሌሎች ስልጠና በመስጠት የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ አሳስበዋል።
ከፌደራል ተቋማት የተውጣጡ ሰልጣኞች በበኩላቸው ያገኙት እውቀት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል።
ከተለያዩ የፌደራል መንግስት ተቋማት የተውጣጡ 110 ሰራተኞች ስልጠናው በኦንላይን ወስደው በማጠናቀቅ ተመርቀዋል።