የዲጂታል አካታችነትን ለመፍጠር ባለደርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ፒ ኤችዲ) ተናገሩ።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 17ኛው የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ከጉባኤው ጎን ለጎን ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ፒኤች ዲ) የዲጂታል አካታችነትን ለመፍጠር ባለደርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

የማይበገር የበይነመረብ ግንኙነት መሰረተ ልማት መገንባት የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ቀዳሚ አጀንዳ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የዘርፉን የኢትዮጵያ የማሻሻያ ስራዎች አብራርተዋል።

ሚኒስትሩ በማይበገር የበይነ መረብ ግንኙት እና ዲጂታል አካታችነት ውስጥ ተሞክሮና ምክረ ሃሳብ የያዘና በዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት የተዘጋጀ የጥናትና ምርምር ሪፖርትንም ኦፊሻሊ መርቀዋል። ጥናቱ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራና ሰራተኛ እንዲሁም ተጋላጭ በሆኑ ቡድኖች ላይ ያተኮረ ሲሆኑ በአፍሪካ፣ ኢሲያ፣ አሜሪካ እና የአረብ ሀገራት ውስጥ ባሉ 17 ሀገራት የተካሄደ ነው።

ዓለም አቀፉ የበይነ-መረብ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ዋናው መክፈቻ በነገው እለት ይካሄዳል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook