የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራተጂ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀደቀ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ስትራቴጂው ኢኮኖሚው የቆመባቸውን ምሰሶች (ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ እና አገልግሎት)፤ ቅድሚያ የተሰጣቸውን ዘርፎች እና በብሄራዊ ደረጃ የተያዙ የስራ እድል ፈጠራ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማሳደግ፣ አካታች ብልጽግና የማረጋገጥ ግቦችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ስትራቴጂው ግብርናው እሴት እንዲጨምር የሚያግዙ የቴክኖሎጂ ስርአቶችን መዘርጋትና መተግበር፤ በግብርና ዘርፍ ቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራን መደገፍ እና ማበረታታት፤ በማምረቻውነ ዘርፍ አዳዲስ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን የመፍጠር እና ጥቅም ላይ ማዋል፤ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሻሻል የሎጂስቲክ ስራ አመራርን በቴክኖሎጂ ማጎልበት፤ ከፍተኛ አቅም እና ተሰጥዖ ላላቸው ማዕከላት መሰረተ ልማት ማቅረብና የመረጃ ቴክኖሎጂ ፓርክን ዳግም በማዋቀር እና በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ በማስገባት የሚሉትን ያካተተ ነው፡፡የቱሪዝም ዲጂታላይዜሽን ግብረ ኃይል በማቋቋም የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ዲጂታላይዝ ማድረግ፣ የቱሪስት ፍሰትን እና የቆይታ እና ተሳትፎ መጠኑን ማሻሻል፤ የቱሪዝም ዘርፍ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የበይነ መረብን ከመጠቀም እና ዲጂታል ክፍያን ከመቀበል አንስቶ ሌሎችንም የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀምን ማጎልበትንም የሚያጠቃልል ነው፡፡

 የዲጂታል ትራንሰፎርሜሽን ስትራቴጂ በሀገር ውስጥ ከሀገር በቀል የምጣኔ ኃብት ተሃድሶ አጀንዳ እና ከአስር ዓመቱ የልማት እቅድ ጋር፤ ከዓለም አቀፍ አንጻር ደግሞ ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች እና ከአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ የዲጂታል ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመና ዘመኑን የዋጀ የምርምር ስልትን ተጠቅሞ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook