በኢኖቬሽንና እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተያዙ እቅዶችን ለማሳካትና ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል በውጭ አገር ተመድበው የሚሰሩ የዲፕሎማቲክ ማሕበረሰብ አካላት እገዛ እንዲያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጺዮን ተክሉ አሳሰቡ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የአዲስ ዓመት የክብር ግብዣ እና የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ለተገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተደርጓል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፂዮን ተክሉ መድረኩ የዘርፉን ተልዕኮ ለመገንዘብና በቴክኖሎጂ ሽግግርና ተያያዥ ጉዳዮች ከአምባሳደሮቻችን ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት የተገነዘብንበት ነው ብለዋል፡፡
በተያዘው ዓመት በኢንቨስትመንት፣ ንግድና ቱሪዝም ዘርፎች የታቀዱትን እቅዶች በቴክኖሎጂ ሽግግርና ምርምር ዘርፎች በማገዝ ውጤት ለማምጣት በዲያስፖራ በተለይም በቆንስላ አገልግሎት (ዜጎችም ጭምር) ሊሳተፉና ሊተባበሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የምክክር መድረኩ በቴክኖሎጂ ወደኋላ መቅረትን ወደ ዕድል መቀየርና መጠቀም ላይ ያለን የግንዛቤ ደረጃን በመረዳት ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር በማምጣት እንዴት መስራት እንደሚቻል መግባባት ላይ የተደረሰበት ነወ፡፡