የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ምርትና አገልግሎት ያላቸውን ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እንደሚደግፍ አስታወቀ።

የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(JAICA) የዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ አማካሪ ሉዑካን ቡድን አባላት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ልኡካኑ በኬኒያ፣ በሩዋንዳ እና በሌሎች አፍሪካ ሀገራት በዘርፉ የሰሯቸውን ስራዎችና ተሞክሮዎችን ያካፈሉ ሲሆን “ቀጣይ ኢኖቬሽን ከጃፓን ጋር” (Next Innovation with Japan – NINJA)የተሰኘውን ፕሮጀክት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ምርትና አገልግሎት ያላቸውን ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችና የግል ዘርፍ ኢንድስትሪን መደገፍ፣ ድርጅቶች እንዲስፋፉ ማድረግና የአቅም ግንባታ መስጠትን የሚያካትት ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ፕሮጀክቱ ከግብ እንዲደርስ በከፍተኛ ጥረትና ትብብር ወደ ስራ እንዲገባ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ እና የጃፓንን የረጅም ጊዜ ትብብር ያነሱት ሚኒስትሩ፣ ጃይካ እና የጃፓን ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ የዘርፉን ስራ እንዲያግዙ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ በተለያዩ መስኮች በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook