የሊንክ ኦል ድርጅት ያለማው ስርዓቱ የሆቴል መረጃዎች ከፀጥታ ተቋማት ጋር እንዲተሳሰሩ የሚያደርግና የፀጥታ ተቋማትን የመረጃ አያያዝ ዲጂታላይዝ ማድረግ የሚያስችል ነው።
በምረቃው ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የዲጂታል የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ የፀጥታ ተቋማትን አሰራር ቀልጣፋ በማድረግ ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
ስርዓቱ የመረጃ አያያዝን ከማዘመን ባለፈ በቂ ሀገራዊ የመረጃ ጥርቅም እንዲኖር በማድረግ የትልቅ ዴታ ትንተና ላይ የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።
የሊንክ ኦል ቴክኖሎጂ አክሲዮን ማህበር መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኑስ አብዱ አህመድ ስርዓቱ በባለድርሻ አካላት ጥናትና ግምገማ ተደርጎበት ለምረቃ መብቃቱን ተናግረዋል፡፡
ስርዓቱ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የሆቴል ባለንብረቶች፣ የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የፖሊስ ተቋማትን እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
ለፍትህ ፣ ለቱሪዝም ፣ ለሰብአዊ መብት ፣ ለሰላም ዘርፎች ጠቃሚ ግብዓቶችንም የሚሰጥ ነው።