ለኢኮኖሚ እድገታችን ዘላቂነት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ተገለፀ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከUNDP ጋር በመተባበር በኢኖቬሽን ስነ ምህዳርና ስራ ፈጣራ ዙሪያ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ፣ ከክልሎች ሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቢሮዎች፣ ከፋይናንስ ተቋማት፣ ከፌደራል እና ከተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናው በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ የፈጠራ ስርዓት ምህዳር ነባራዊ ምንነት፣በጀማሪ የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣራዎች አካታች ፕሮግራም ትግበራ እና አመራር፣በዘርፉ ያሉ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ፣ የኢንተርፕርነርሺፕ እና የፈጠራ ፕሮግራሞች፣ የእሴት ፈጠራ ልምምድ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ በይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) የቴክኖሎጂ ክምችት እና የፈጠራን ሀሳብ የሚያበረታታ ስርዓት በመዘርጋት ይህንንም በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ሊያስፈጽም የሚችል የሰው ሀብት ልማት ላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በጥናትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ እድገትና ሽግግር እንዲሁም ፈጠራ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን የሚገኙት የተፈጥሮ ሀብቶች በቴክኖሎጂ በመደገፍ ያለውን የኢኮኖሚ ችግር ለመፍታት እንደሚሰራም አብራርተዋል።