ዲያስፖራው በቴክኖሎጂ ዘርፍ የዓለም አቀፉን የገበያ ፍላጎት ታሳቢ ባደረገ ስራ ላይ እንዲሰማራ ተጠየቀ፡፡

ዲያስፖራውን በቴክኖሎጂ ዘርፍ የቢዝነስ አማራጮች እንዲሰማራና በሀገር ውስጥ ካሉ ባለሙያዎች ጋር እንዲተዋወቅ የሚያደርግ የግፀ-ለገፅ እና የበይነ መረብ ቅይጥ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ዲያስፖራው የውጪ ምንዛሬ በሚያስገኝ፣ ለወጣቶች የስራ እድል በሚፈጥርና የዓለም አቀፉን የገበያ ፍላጎት ታሳቢ ባደረገ ስራ ላይ እንዲሰማራ ጠይቀዋል፡፡

መንግስት በግሉ ዘርፍ የሚመራ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በትኩረት እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የግሉ ዘርፍ እና ዲያስፖራው በዘርፉ ለሚያደረጉት እንቅስቃሴ ሁሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ለመምከርና የዲያስፖራ ቴክ ፎረም ለመመስረት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው መድረክ ላይ እንዲሳተፉም ለዲያስፖራው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

“ዲያስፖራውን ከሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ጋር ማገናኘት” በሚል “ፓርትነር ፎር ቼንጅ” ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት፣ የግሉ ዘርፍ አንቀሳቃሾች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና የመንግስት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የዲጂታል የስራ እድል ፈጠራ እየሰፋ በመምጣቱ ወጣቶችን ለዚህ ሰራ ዝግጁ ማድረግ አንደሚገባ እና በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑ ተነስቷል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook