ፓኪስታን “የኢትዮ-ፓኪስታን ሳይንትፊክ ዲፕሎማሲ ፎረም” እንዲመሰረት ጥያቄ አቀረበች።

ፎረሙ በሳይንቲፊክ ጉዳዮች ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ልምድ እንዲለዋወጡና በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል ነው።

በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሾዛብ አባስ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ሁለቱ ሀገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

አምባሳደሩ በአካባቢ ጥበቃ እና በውሃ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምርምር የሚያደርግና የእውቀት ሽግግር የሚፈጥር “የኢትዮ ፖኪስታን ሳይንቲፊክ ዲፕሎማሲ ፎረም” እንዲመሰረት ጠይቀዋል።

ኢስላማባድ የሚገኘው COMSATS ዩኒቨርሲቲና የፓኪስታን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ከሳይንስና ክፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የሚሰሩባቸው አሰራሮች በሚዘረጉበት ሁኔታ ላይም መክረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ (ፒ ኤች ዲ) ፎረሙ እንዲመሰረት ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉና ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ያደረገቻቸውን የማሻሻያ ስራ ልምዶች ለፖኪስታን ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

የእስያ ሀገራት የዲጂታል እውቀት ላይ የተሻለ ልምድ ስላላቸው ኢትዮጵያም ከፓኪስታን ያሉ ልምዶችን ትወስዳለች ብለዋል።

በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሾዛብ አባስ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ እየሰጡት ላለው ትክክለኛ መረጃ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook