ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታ መፍጠር የሁላችን ሀላፊነት ሊሆን ይገባል:- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ)

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከUNDP ጋር በመተባበር በኢኖቬሽን ስነ ምህዳርና ስራ ፈጣራ ዙሪያ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እና አመራሮች በተከታታይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ በይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታ መፍጠር የሁላችንም ሀላፊነት ሲሆን ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት የሀገራችን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን እድገት በቴክኖሎጂ መመራት አለበት ብለዋል።

ለእርሻ ስራና ምርት ወሳኝ የሆኑት በእጃችን ያሉ ሀብቶች የዘመነ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ባነሰ ሰው ሀይልና እጅግ ባጠረ ጊዜ በርካታ ምርት ለማምረት የቴክኖሎጂ አቅማችንን ማሳደግና ተፈጥሯዊ ሀብታችን ለጥቅም የሚውልበት መንገድ ምቹ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጀማሪ የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣራዎች እና የኢንተርፕርነርሺፕ የተሰጠውን ስልጠና ወደ ተግባር ተቀይሮ ውጤት እንዲያፈራ ሰልጣኞች ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ስልጠናው ቀጣይ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙት ባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook