በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የቀጣይ መቶ ቀናት እቅድ የቡራዩ ታለንት ልማት ኢንስትቲዩትን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል ተባለ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ በለጠ ሞላ አዲስ ከተሾሙት ሚኒስትር ዲኤታዎችና ከተቋሙ አጠቃላይ የስራ አመራር ጋር በመሆን የቡራዩ የታለንት/ተሰጥኦ ልማት ማእክልን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የማእከሉ ዓላማ፣ የግንባታ ሂደት፣ ግንባታው የደረሰበት ደረጃና ያጋጠሙ ችግሮችን የተመለከተ ማብራሪያ ከፕሮጀክት አማካሪዎች፣ ከተቋሙ ወኪሎች ለክቡራን ሚኒስትሮች ተሰጥቶአል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምርምር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒኤችዲ) በርካታ ተግዳሮቶችን በማለፍ ፕሮጅክቱን ለማጠናቀቅ የተደረገውን ጥረት ከጉብኝቱና ከማብራሪያው መረዳታቸውን አውስተዋል፡፡

እንደ ዶክተር ባይሳ ከመንግስት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ፕሮጀክቱን በቀጣይ መቶ ቀናት ካቀድናቸው ተግባራት በቅደሚያ በማጥናቀቅ ለታለመለት ዓላማ ዝግጁ ለማድረግ በዘርፋቸው ቅድሚያ ሰጥተነዋል ብለዋል፡፡

የአይሲቲ ልማትና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ሁሪያ ዓሊ በበኩላቸው በጉብኝታችው ባዩት የፕሮጀክቱ ደረጃ መደሰታቸውን ጠቁመው፤ የኛ ስራ ቴክኖሎጂ ማበልጸግ ብቻም ሳይሆን ተሰጥኦዎችን ማበልጸግም በመሆኑ መሰል ተቋማት መጀመራቸው ሊበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡

እንደ ክብርት ሁሪያ የፕሮጀክቱን መጓተት ለማሰቀረት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትራችን ያገኘነውን አርዓያነት ተጠቅመን በማጠናቀቅ ለቃላችን ታማኝ ሆነን መገኘታችንን ማሳየት አለብን ብለዋል፡፡

ክቡር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ በለጠ ሞላ በበኩላቸው የተመለከቱት ፐሮጀክት ግዙፍና ሊያሳካው የታለመለት ዓላማም ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

ይህን አገራዊ ፋይዳው የጎላ ግዙፍ ፕሮጀክት በርካታ መዘግየቶችን ያጋጠሙት መሆኑን ተገንዝበናል።

ግንባታው ቸተጓተተ ቢሆንም አሁን የደረሰበት ደረጃ ሲታይ በተቀመጠለት የመጨረሻ መርሃ ግብር ከተጠናቀቀ አበረታች ነው፡፡

በጉብኝቱ ጥራትን ለማስጠበቅ የተደረገውን ጥረት ማስተዋላቸውን ያመሰገኑት ክቡር ሚኒስትሩ ፕሮጅክቱ ጥራትን ከጋዜ ጋር ማጣመር ስላለበት ከዚህ በላይ እንዲጓጓተትና እንዲዘገይ ሊፈቀድለት አይገባም ሲሉ በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

ትልልቅ አገራዊ ጉዳዮችን በተቀመጠላቸው ጊዜ ተፈጽመው ለሕዝብ ጥቅም እንዲውሉ መስራት የሁላችንም ድርሻ ስለሆነ ሁላችንም ኮንትራት ወሰደናል ያሉት ክቡር አቶ በለጠ ሞላ፤ በዚህ ፕሮጅክትም ፊዚካል ስራው በተቀመጠለት የመጨረሻ ጊዜ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ ሊውል ይገባል።

በመሆኑም አስፈላጊውን ሁሉ በማደረግ ለቀጣይ የእቅድ ሰራዎቻችን ስኬት የሚሆን ስንቅ በሚሆን መልኩ ልንፈጽመው ይገባል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ከፊዚካል ስራዎች ጎንለጎን ስራ መጀመር የሚያስፈልጉት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ሁሉ እንዲደረጉም መመሪያ የሰጡት ከቡር ሚኒስትሩ የፕሮጀክቱ ስኬት ለቀጣይ መሰል ፕሮጀክቶች የሚሰፋ አቅም በሚያስገኝ መልኩ ተጠናቆ ስራ መጀመር አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ይህ ፕሮጀክት በርካታ ተገዳሮቶችን አልፎ እንዲጠናቀቅ በክቡር ከንቲባው የተሰጠውን ትኩረት መገንዘባቸውን ያወሱት ከቡር አቶ በለጠ በቀጣይም ተቀራርበን የምንሰራበትን አቅም በማስገኘቱ ከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የልዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ እና በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኮምፒውቴሽናል መስኮች ከፍተኛ ችሎታ ያላቸውን ዜጎች በልዩ ሁኔታ ለማልማት ታስቦ ማእከሉ እየተገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook