የኢንስቲትዩት ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ ለምረቃ በዓል የሚሆኑ የፈጠራ ሞዴል ስራዎችን የሚያቀርቡ የተመረጡ የፈጠራ ባለሙያዎችን በተቋሙ ተቀብሎ ድጋፈው በማድረግ ስራዎቻቸውን እንደያበለፅጉ እየተሰራ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒኤችዲ) ከፈጠራ ባለሙያዎች ጋር መክረዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት በሀሳብ የተጀመረውን ወደ ውጤት በመቀየር በቀጣይ ቅበላ ለሚደረግላቸው የልዩ ተሰጦና ተውቦ ተማሪዎች ሞዴል የሚሆኑ ስራዎችን ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው የፈጠራ ባለሙያዎችን አሳስበዋል፡፡
“አይቻልም” የሚባሉ ስራዎች እንደሚቻሉ ማሳየት የምንችልበትን ሂደት በመፍጠር የፈጠራ ውጤቶችን ወደ ሀብት በመቀየር፣ የተክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ፣ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በማዘመን፣ የስራ እድል በመፍጠርና ከውጪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን በራሳችን በመተካት የድህነትን ጊዜ ልናሳጥር ይገባልም ብለዋል፡፡

የተመረጡት የፈጠራ ባለሙያዎች በስፔስ ቴክኖሎጂና ጂኦስፓሻል እንዲሁም በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ የምርምር ተቋማት ጉብኝት አድርገዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሂርፓሳ ጫላ (ፒኤችዲ) የፈጠራ ባለሙያዎችን በመደገፍ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ባለቤት መሆን የሚያስችለንን ስራ እንሰራለን ብለዋል።
የተቋሙ ስራ መጀመር በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን በመሰብሰብ፣ በማብቃት፣ ወደ ውጤት በመቀየርና የስራ ዕድል በመፍጠር ኢትዮጶያ ያላትን ብዙ የወጣት ሀይል ሀብት መጠቀም የምትችልበትን ስርዓት ይፈጥራል፡፡
የፈጠራ ባለሙያዎቹ ከጉብኝቱ ብዙ ነገር እንዳገኙ ጠቅሰው እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ አቅም ከመፍጠሩም ባለፈ ስራቸውን ወደ ውጤት መቀየር እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል፡፡