የተከለሰው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ወደ ስራ ገባ።

ፖሊሲው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋና ዋና ግቦች፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ሀገራዊ ምርትን ማሳደግ፣ አዳዲስ ሀብት መፍጠር እና አካታችን ይዞ የተከለሰ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) የተከለሰውን ፖሊሲ በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

የተከልሰው ፖሊሲ በቴክኖሎጅ የታገዝ ፈጣን ኢኮኖሚን ለመገንባት፣ የሰለጠነ እና ብቁ የሰው ኀይልን ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ምርምር እና ልማት፣ የቴክኖሎጂ ልማት ሽግግር፣ የዕውቀት አሥተዳደር፣ የኢኖቬሽን እና ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ አካባቢያዊ እና ባህላዊ ልማት በዋናነት ፖሊሲው ሊተግብራቸው ያሰባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ሚያዝያ 2014ዓ.ም በሚንስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ይህ የተከለሰው ፖሊሲ የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን፣ የአፍሪካ 2063 አጀንዳንና 2024 የሳይንስ፡ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስትራቴጂን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጀ የመደራደር አቅም ያለው የሰው ሃይል እንዲገነባ፣ ልዩ ተሰጥኦና ተውህቦ ላለቸው ዜጎች እንዲሁም በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የሙያ ዘርፎች በቂ እና ብቁ በለሙያዎችን ገበያና ቴክኖሎጂ ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ ማፍራት በፖሊሲው ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook