የአፍሪካ ሀገራት የወጣቶቻቸውን አቅም ለመጠቀም የሚያስችል ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታ መፍጠር ይኖርባቸዋል:- ሁሪያ አሊ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ

7ኛው የአፍሪካ የስራ ፈጠራና ኢኖቬሽን ጉባኤ በበይነ-መረብ ተካሂዷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የአፍሪካ ሀገራት የወጣቶቻቸውን አቅም ለመጠቀም የሚያስችል ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታ መፍጠር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

አፍሪካ ከ250 ሚሊየን በላይ ወጣቶች አሏት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የዚህን ወጣት አቅም አሟጥጦ ለመጠቀምና የቴክኖሎጂ መፍትሄ አፍላቂ እንዲሆኑ ለማድረግ መንግስታት በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር መኖር፣ ተፈትኖ የተረጋገጠ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት፣ የቴክኖሎጂ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በመንግስት በኩል ያለ ቁርጠኝነት በዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀሱ ናቸው።

በጉባኤው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት የስራ ፈጣሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook