የኢኖቨሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ( UK) ኢምባሲ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር በለጠ ሞላ (ፒ.ኤች.ዲ) በኢትዮጵያ የየዩናይትድ ኪንግደም ብሪታኒያ ኢምባሲ አምባሳደርን ዶክተር አላስቴር ማክፌይልን በቢሯቸው ተቀብለው አወያይተዋል።

ዶክተር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያና የUK/ብሪታኒያ አገራት የረጅም ዘመናት የቆዬ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን አውስተው ይህን ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ መስክኮች ማጠናከርና ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸውላቸዋል።

በተለይም አገረ እንግሊዝ(UK) በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ የካበተ ልምድና እውቀት ከሚገኝባቸው አገራት አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትሩ የዘርፉን የዳበረ ልምድ ለኢትዮጵያ ለማጋራት የሚደረጉ ድጋፎችና ትብብሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አልስቴር ማክፌይል በበኩላቸው አገራቱ ያላቸውን በመልካም የሚጠቀስ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቁመው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የልማት እና ትብብር ድጋፎችን ስታደርግ መቆየቷን አውስተዋል።

ወደፊትም መተባበር የሚቻልባቸውን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን በመለየት ድጋፍ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።

በተጨማሪም የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በትኩረት እየተከታተሉት እንደሆነ የጠቆሙት ክቡር አምባሳደሩ፤ ሁኔታው በአገራዊ የምክክር መድረክ ሊፈታ የሚችልበት እድል እንደሚፈጠር ያላቸውን እምነት ለክቡር ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር በለጠ ሞላ (ፒ.ኤች.ዲ) በበኩላቸው ክቡር አምባሳደሩ ወቅታዊ ሁኔታውን አስመልክቶ ያነሱትበን መነሻ እንደሚገነዘቡት ገልጸው መንግስት በአገራዊ ሁኔታው ላይ ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት አበክሮ እየሰራ መሆኑን አብራርተውላቸዋል፡፡

ክቡር አምባሳደር ዶክተር አልስቴይር በአገራቱ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር አገራቸው በቀጣይ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቅሰው በሌሎች የትብብር ዘርፎችም በመደጋገፍ መስራት እንደሚገባ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር በጥልቀት ተወያይተዋል፡፡

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook