የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከራያ የተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በድሬ ሮቃ ለሚገኙ ወገኖች የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ሚኒስቴሩ ከአጋር አካላትና ከተቋሙ ያሰባሰበው የአልባሳትና ምግብ ድጋፍ ከራያ የተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ለሚገኙ ወገኖች የሚውል ሲሆን የ 6.5 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ነው።

ድጋፉን ያስረከቡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) ድጋፉ ወራሪው የትሕነግ ቡድን በፈጠረው ችግር እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወገኖች ሊደረግ ከሚገባው እጅግ ትንሹ ነው ብለዋል።

ቦታው ተገኝተን እንደተመለከትነው አቅርቦቱ ከችግሩ ስፋት አኳያ በጣም ትንሽ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዓላማችን የወገናችንን ስቃይና ስሜት ከመጋራት ባለፈ የችግሩን ስፋት ለመላው ዓለምና ለሚመለከታቸው ለማሳየትም ነው ብለዋል።

በድሬ ሮቃ ከራያ የተለያዩ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ብቻ ሳይሆኑ በአፋኙ የህወሃት ቡድን ስር ከሚገኙ የትግራይ አካባቢዎም ጭምር የመጡ ይገኛሉ።

ሁሉም አካላት የበኩላቸውን በማድረግ የንጹሃን ወገኖቻችን ስቃይ እንዲጋራና እንዲረዳ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዋግ ኸምራ ዞን ለሚገኙ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖችም ተመሳሳይ የአልባሳትና የምግብ አቅርቦት ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook