የጅማ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እየሰራ ያለውን ስራ ሌሎች በአርአያነት ሊወስዱት እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) ከጂማ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ዩኒቨርሲቲው የህክምና መሳሪያዎችን በራሱ አቅም በመንደፍና (design) በማምረት ወደ ገበያ ጭምር የገቡ መኖራቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ (ፒ ኤች ዲ) ተናግረዋል።

የተወሰኑ የክሊኒካል ሙከራ ላይ ያሉ መኖራቸውንና በቅርቡም ወደ ምርት እንደሚገቡ ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ ከተወሰኑ እቃወች ውጭ ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ አቅም የተሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂው ዘርፍ የፈጠረው አቅም ለሌሎች መማሪያ እንዲሆን በቅርብ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችን በዩኒቨርሲቲው ክላስተር ስር ማደረጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ከውጭ የሚመጡ እቃዎችን በሀገር ውስጥ መተካት የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ይረዳል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ወደ ገበያ ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት ሚኒስቴሩ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።

የዲዛይንና የሞለኪዩላር ላብራቶሪን የጎበኙት አመራሮቹ የዩኒቨርሲቲውን የሶቫልና የቴክኖሎጂ ኢኖቬሽንን ወደ አንድ በማምጣት ድጋፍ ለማድረግና በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል።

አመራሮቹ በቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ የኢትዮጵያን እናልብስ መርሃግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ በማከናወን የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook