የግል ዳታ ጥበቃ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው። ኢትዮጵያም የዜጎቿን የግል ዳታ ለማስጠበቅ ይረዳት ዘንድ ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ እያረቀቀች ትገኛለች።

ቀኑ በየአመቱ ጥር 20 የሚከበር ሲሆን በግል ዳታ ጥበቃና ደህንነት ዙሪያ ለግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና የንግድ ተቋማት ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚከበር ነው።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ ሰዎች የመረጃ ልውውጣቸውንና የገንዘብ ዝውውራቸውን በዲጂታል መልኩ እያደረጉ ነው።

የግል ዳታ አቀናባሪዎችና ተቆጣጣሪዎች ደግሞ የግል ዳታን ይሰበስባሉ፣ ይመዘግባሉ፣ ያደራጃሉ፣ ያዋቅራሉ፣ ያከማቻሉ፣ ይጠቀማሉ፣ በተለያዩ መንገዶ እነዚህን ዳታዎች ለሶስተኛ ወገኖች ይፋ ያደርጋሉ።

እነዚህ አካላት የግል መረጃን ሲያቀናብሩ የግል ዳታ ማቀናበር መርሆዎችን ባከበረና የባለቤቶቹን መብት በጠበቀ መልኩ መሆን ይገባል። ኢትዮጵያም የዜጎቿን የግል ዳታ ለማስጠበቅ ይረዳት ዘንድ ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ እያረቀቀች ትገኛለች።

ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት መኖር ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለፋይናንስ፣ ለትራንስፖርት ዘርፍ መጎልበት ትልቅ ጠቀሜታ አለው።

መንግሥት ለዜጎች የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ተደራሽነት ያሰፋል፤ ዕንግልትን ይቀንሳል፣ በሂደትም ያስቀራል፣ ተዓማኒነቱንም ከፍ ያደርጋል።

በአደጉ ሀገራት ያሉ የዳታ ተቆጣጣሪዎች የያዟቸውን የግል ዳታዎች በኢትዮጵያ እንዲቀናበር ሁኔታዎችን በማመቻቸት ኢንቨስትመንትን ያበረታታትል፣ የሥራ ዕድልንም ይፈጥራል።

ኢትዮጵያ የግል ዳታ ጥበቃ ሥርዓት በመፍጠር፣ ለግል ዳታ ጥበቃ የነቃ ዜጋን በማፍራት፣ የግል ዳታ ጥበቃን የሚያረጋግጡ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀምን ባህል በማጎልበትና ዓለም አቀፍ ትስስርን በመገንባትና በማስፋት የዲጂታል ኢኮኖሚን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም እየሰራች ትገኛለች።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook