ጉባኤው የተለያዩ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላት ከኢንተርኔት ጋር የተያያዙ ፖሊሲዎች ላይ ውይይት የሚያካሂዱበት መድረክ ነው።
ኢትዮጵያን በመወከል እየተሳትፉ ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂና ትግበራ ልምድ ለመድረኩ አካፍለዋል።
በተለይም የዲጂታል ኢኮኖሚ የሕግ ማእቀፎችን ከማዘጋጀት እና የተቋማት ትስስርን ከመፍጠር አንጻር የተከናወኑ ስራዎችን አብራርተዋል።
በቀጣይ አመት የሚካሄደው 17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ከኢንተርኔት ጋር ተያይዞ ያሉ ዕድሎችን እንዲሁም ፈተናዎችና ተግዳሮቶችን በተመለከተ የሚነሱ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበትና የጋራ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መድረክ ነው፡፡