222 የመንግስት አገልግሎቶች ኦንላይን እየተሰጡ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባለማቸው ስርዓቶች ውስጥ የሚተገበሩ 222 አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ ነው። በትላንትናው እለትም 45 የመንግስት አገልግሎቶች ኦንላይን ለመስጠት የሚያስችሉ ስርዓቶች ለምተው ተመርቀዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጋር አገልግሎቶቹ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲተገበሩ ለማድረግ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራመዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የመንግስት አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ለማድረግና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይ 10 አመት ውስጥ 2,500 አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት እቅድ መያዙን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ 222 አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ መሆናቸውንና ከ100ሺ በላይ ዜጎች ደግሞ በስርዓ ውስጥ መመዝገባቸውን አብራርተዋል።

በዚህ አመት 400 የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ ነው። የመንግስት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት የሚሰጥበትን ፖርታል ከ1.7 ሚሊየን በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል።

ይህንን ልጥፍ ያጋሩ

Share on twitter
Share on linkedin
Share on facebook