
ስኬቶች
ስኬቶች
ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ ማድረግ
የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ፣ የብሔራዊ ድጅታል ስትራቴጂ መዘጋጀቱ፣
ሚኒስቴሩ የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠናን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ዲጂታል መታወቂያ ለማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል፡፡ በስርዓቱ ውስጥ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ እና የፋይናንስ ስርዓትን በሙሉ አካቶ የሚይዝም ጭምር ነው፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱኢ-ኮሜርስ
ዓለም በኢንተርኔት ገበያ ውስጥ ከፍተኛ ገንዘብ በሚያንቀሳቅስበት በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ውስጥ በዚህ ዘርፍ እምብዛም እንቅስቃሴ አይደረግም፡፡ የኢንተርኔት ገበያውን ለመቀላቀልና የግብይት ስርዓቱን ቀልጣፋ ለማድረግ ኢትዮጵያ ውስጥ የምስራቅ አፍሪካ የኢ-ኮሜርስ ማዕከል ለመግንባት ታቅዷል፡፡ ኢትዮጵያ የግብይቱ መተላለፊያ ኮሪደር ሆና የምታገለግል ሲሆን ስርዓቱ ወደ ስራ ሲገባ ለ100ሺዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርና በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖር ያስችላል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱየተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት
ሚኒስቴሩ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የዘረጋውን የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት አስመርቆ ለሆስፒታሉ አስረከቧል፡፡ ስርዓቱ የታካሚዎችን እንግልት በማስቀረት የሃኪሞችን ድካም ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ነው፡፡ አገልግሎቱ ሃኪሞች የታካሚዎቻቸውን መረጃ ለመፃፍ በእጅ ፅሁፍ መልክ የሚፅፉበት በሀገራችን ወጣት ባለሙያዎች ዲዛይን በተደረገ ታብሌት ታግዞ ስራ ላይ ይውላል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱበሬን የሚተካ ዘመናዊ ማረሻ
በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዲዛይን ተደርጎ የተሰራውና በእጅ የሚገፋ ዘመናዊ ማረሻ በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ "በሬ ለምኔ" የሚል መጠሪያ የተሰጠው ማረሻው የአርሶ አደሮችን ድካም በመቀነስ እርሻቸውን ለማቀላጠፍ ከማስቻሉ በተጨማሪ አርሶ አደሮች ለእርሻ የሚጠቀሙባቸውን በሬዎች በማድለብ ወደ ስጋ ገበያ በመቀየር ገቢያቸው እንዲጨምር ያግዛል።
ተጨማሪ ይመልከቱሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን)
በሀገራችን ገጠራማ አካባቢዎች እስከ 5 ኪ.ግ የሚደርሱ መድሃኒቶችን ለማጓጓዝና ለማድረስ የሚያስችል ሰው አልባ አውሮፕላን ተሰርቶ የተሳካ ሙከራ ተደርጓል፡፡ በ5ሺ ሜትር ከፍታ 120 ኪ.ሜ በሰዓት የመብረር አቅም ያላት አውሮፕላኗ ደርሶ መልስ 300 ኪሜ ርቀትን ትሸፍናለች። የትራንስፖርት እጥረት ባለባቸው አስቸጋሪ ቦታዎች የህክምና ቁሳቁሶችን ለማድረስ ታስባ የተሰራች ናት፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱክላውድ ኮምፒውቲንግ
ልዩ ልዩ መረጃዎች የሚከማቹበት ቦታ እና የኮምፒውተር ንብረቶችን መገናኘት የሚችሉበት የደንበኝነት ምዝገባ ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ነው፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዳመና ማስላት ቴክኖሎጂ ተግባራዊ በማድረግ የተለያዩ የሳይንስ ተቋማትን በማስተሳሰር ቀደም ሲል የነበረውን ኋላ ቀር አሰራር ለማስቀረት መረጃን ከአንድ የመረጃ መረብ ክምችት በመጠቀም የነበሩትን ውጣ ውረዶችና ችግሮች ማስቀረትና የተቀላጠፈ ስራን በመስራት ከጊዜው ጋር እንዲጓዝ የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱየኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢግዚቢሽን/ትዕይንተ ማዕከል
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የራሱን እንቅስቃሴዎችና ዓለም ዓቀፍ ጥዕይንቶንን የሚሳይበት በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የበለጸገ የኢግዚቢሽን ማዕከል በመገንባት ዓለም የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ገጸበረከትን ለእንግዶች ሁሉ በማስጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡ የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ጉዟችን በማዕከሉ ውስጥ ለእይታ ወደ ቀረቡት ቴክኖሎጂዎች መሆን አለበት ብሎ እየሰራም ነው፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱየዲጂታል ቪዲዮ ኮንፈረንስ ማዕከል
የቪዲዮ ኮንፈረንስ ቴክኖሎጂ ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ ማንኛውንም ግንኙነት (ሰሚናር፤ ስብሰባ፤ አውደ ጥናት…) በአንድ ቦታ ሆኖ ለማሳለጥ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ቪዲዮ ኮንፈረንስ ማዕከል በማደራጀት እየተጠቀመ ይገኛል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱየኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ የቴሌቪዥን ብሮድካስቲንግ ማዕከል
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሃገራችን በዓይነቱና በይዘቱ የመጀመሪያ የሆነ የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ የቴሌቪዥን ብሮድካስቲንግ አገልግሎት በመጀመር በህብረተሰቡ ዘንድ የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ ባህልን ለማስረጽ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱ
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ተውህቦ እና ሃሳብ ማበልፀጊያ ማእከል
ማእከሉ ልዩ ተሰጥኦና ችሎታ ያላቸውን ዜጎች በመለየት የቴክኖሎጂ ጥማታቸውንና ፍላጎታቸውን እውን ለማድረግ የሚማሩበትና የሚበለጽጉበት ሲሆን በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልልዊ መንግስት በቡራዩ ከተማ ውስጥ ግንባታው ተጀምሯል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱየሳይንስ ካፌዎች
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሀገራዊ ሳይንሳዊ እና ቴክኖሎጂካዊ አስተሳሰብንና ባህልን ለመገንባት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች የሳይንስ ካፌ በማቋቋም ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት የሳይንስ ካፌዎችን ገንብቷል፡፡ እየገነባምይገኛል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱየኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሀብ
አሁን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በሚገኝበት ሕንፃ ዙሪያ የሚገኘውን 3.2 ሄክታር የሚሸፍን ቦታ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መገኛ ማዕከል ማድረግ እንዲቻል ከአዲስ አበባ መስተዳደር የይዞታ ማረጋገጫ ካርታማግኘት የተቻለ ሲሆን ከቦታው ለሚነሱት የካሳ ግምት ሥራና ቦታው ላይ የሚያርፉ በቁጥር 8 ሕንፃዎች የዲዛይን ስራ ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱኤች ፒ ሲ
በኢንጂነሪንግ፣ በሳይንስ፣ በቢዝነስና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ መረጃን ለመተንተን የሚያስችል አቅም በመፍጠር ያሉብንን ችግሮችን ለመፍታት ሃይ ፕሮርማንስ ኮምፒውቲን /High Performance Computing/የ200 ቴራ ፍሎፒ /200 TF HPC/ አቅም መገንባት ወሳኝ በመሆኑ ትልልቅ መረጃዎችን መተንተን የሚስችል አቅም እየገነባ ይገኛል፡፡ ይህ የቴክሎጂ አቅም የሀገር ውስጥ ተመራማሪዎች ትላልቅ መረጃዎችን በሀገር ውስጥ እንዲተነትኑ በማስቻል ወደ ውጭ ልከው በሚያስተነትኑበት ጊዜ የሚወጣውን የጊዜ እና ገንዘብ ብክነትን ይቀንሳል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዢ ሥርዓት(e-GP)
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዢ ሥርዓት (e-GP) እና የአፈፃፀም ስትራቴጂ በፋይናንስ ሚኒስቴር በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ይፋ ሆኗል፡፡ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የበለጸገው አሰራር የግዢና የፋይናንስ ስርዓቱን እንደሚያዘምነው ታምኖበታል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱ